Aman Properties blog

From the
Aman blog

Guidesአማርኛ

ሪል ስቴት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ?

7 October 2026 · 2 min read · Aman Properties

ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና ሶሻል ሚዲያ ላይ በሚነገሩ ማስታወቂያዎች እንዲሁም በየመንገዱ በምናገኛቸው የሽያጭ ባለሙያዎች አፍ ላይ የምንሰማው አንድ ቃል አለ። ሪል ስቴት!

ለመሆኑ ግን ሪል ስቴት ማለት ምን ማለት ነው? የአማርኛ አቻ ፍቺስ አለው?

መሬትን ጨምሮ ከመሬት ጋር ተያይዞ የተገነባ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት በአጠቃላይ ሪል ስቴት ይባላል። እስካሁን ድረስ ሀሳቡን የሚገልጽ አጭር የአማርኛ ቃል ባለመኖሩ የእንግሊዘኛ አቻው በስፋት አገልግሎት ላይ ይውላል። 

የግለሰብ መኖሪያ ቤት፣ ህንጻ፣ አፓርትመንት፣ የንግድ ቦታ እና መሬት ሪል ስቴት የሚለው ጥላ ውስጥ ሲካተቱ በተቃራኒው መኪና፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ልብስ ወይም ጌጣጌጥ እና የመሳሰሉት እንደ ተንቀሳቃሽ ንብረት ስለሚቆጠሩ ሪል ስቴት አይባሉም።    

ታዲያ ሪል ስቴት በተለምዶ እንደምናየው እና እንደምንሰማው ቤት መግዛትና መሸጥ ብቻ ነው?

በፍጹም አይደለም።

ባዶ መሬት ላይ አንድ ቤት ወይም ህንጻ ተገንብቶ ለገዢው እስኪደርስ ድረስ ከበስተጀርባው ብዙ ሂደቶችን ያልፋል። የመሬት ልማት፣ የፕሮጀክት እቅድ፣ ዲዛይን፣ ግንባታ፣ ፋይናንስ፣ ሽያጭ እና የንብረት አስተዳደርን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎችን እና ስራዎችን በውስጡ ያካትታል።

እነዚህን ሁሉ ሂደቶች አንድ ድርጅት ብቻውን አይሰራውም። አልሚዎች፣ አርክቴክቶች፣ ኢንጂነሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሽያጭ ባለሙያዎች እና ገዢዎች የሪል ስቴት ዘርፍን አንድ ላይ የሚያስኬዱ ተሳታፊዎች ናቸው። 

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ሪልስቴት ከ30 አመታት በላይ የቆየ ታሪክ ያለው ዘርፍ ቢሆንም ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ግን ብዙ ውጣውረዶችን አልፏል። በገቡት ቃል መሰረት በጊዜ እና በጥራት ማስረከብ ባልቻሉ አልሚዎች አማካኝነት “ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ“ እንዲል የአገር ሰው ታማኝ የሪልስቴት አልሚዎችንም ጨምሮ ዘርፉ ስሙ ጠፍቶ ቆይቷል። ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን እንደ አማን ፕሮፐርቲስ ባሉ ይሄንን ውዥንብር ማጥራት በቻሉ አልሚዎች አማካኝነት ዘርፉ እንደገና ስሙን ማደስ ጀምሯል። የከተሞች እድገት እና እየጨመረ የመጣው የመኖሪያ ቤት ፍላጎትም ዘርፉ እንዲነቃቃ ካደረጉት ምክንያቶች መካካል ዋነኞቹ ናቸው። 

ስለ ቤት አቅርቦት ካነሳ አይቀር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሪልስቴት አልሚ ድርጅቶች ባሉባት ኢትዮጵያ ካለው የቤት አቅርቦት ፍላጎት ጋር ሲነጻጻር እስካዛሬ የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ መኖሪያ ቤቶች የአቅርቦት ፍላጎቱን በግማሹ እንኳን ማሟላት አለመቻላቸው ዘርፉ ገና ረጅም ርቀት መጓዝ እንደሚኖርበት ያመላክተናል። 

በተለይ በአዲስ አበባ ብቻ ተገድቦ የቆየው ይህ ዘርፍ ወደ ክልል ከተሞችም በመግባት አንገብጋቢ የሆነውን የቤት አቅርቦት ፍላጎት ለሁሉም ማዳረስ ይኖርበታል።

አማን ፕሮፐርቲስም በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰፋፊ መሬቶችን በመረከብ እና ዘመናዊ ቤቶችን በመገንባት በዚህ ዘርፍ የበኩሉን አሻራ ለማሳረፍ እና የቤት አቅርቦት ፍላቱን ለማዳረስ እየሰራ ይገኛል። ወደፊትም ወደ ክልል ከተሞች ትላላቅ ፕሮጀክቶችን ይዞ ለመስራት አቅዷል። 

ሪል ስቴት የሚለው ቃል ከምናየው የሽያጭ ማስታወቂያም በላይ ሰፊ ነው። 

ከአንድ ጠጠር እና ሚስማር የሚጀምር አንድ ፕሮጀክት ብዙ ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ ፣ ብዙዎች የሚኖሩበትን ፤ የሚሰሩበትን እና የሚያተርፉበትን ንብረት የሚፈጥር ፤ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አሻራ ያለው ሰፊ ዘርፍ ነው። 

 የዛሬ ጦማራችን በዚህ ያበቃል። 

በኢትዮጵያ ያለውን የሪል ስቴት ዘርፍ ይበልጥ ለመረዳት የሚያስችሉ ጦማሮችን እዚሁ ዌብሳይታችን ላይ በቀጣይነት የምናቀርበው ይሆናል። እስከዚያው በአማን ይቆዩን!

← All articles

We are open

Talk to us today

Call, message or visit the sales office at Laphto Mall — we reply the same working day.

Call us
+251 945 59 59 59
Call short code
8077
WhatsApp
Message us
Email
info@amanpropertiesaddis.com
☎Call ✉WhatsApp ✎Book