የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር የ20 ሚሊየን ቤት ሽልማት ከአማን ፕሮፐርቲስ ሊሸለም ነው!!!
በጂ ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር የ20 ሚሊየን ቤት ሽልማት ከአማን ፕሮፐርቲስ ሊሸለም ነው!
በአገራችን ኢትዮጵያ የጥበብ ሰዎችን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ጥረታቸውን፣ የፈጠራ አቅማቸውንና ችሎታቸውን የሚያበረታቱ የተለያዩ የሽልማት መድረኮችን ተመልክታችኋል፣ አይደል?
በእነዚህ መድረኮች ላይ እስካሁን ያያችሁት ወይም የሰማችሁት ትልቁ ሽልማት ምንድን ነው?
መኪና ወይም የገንዘብ ሽልማት እንደምትሉ አንጠራጠርም። ደግሞም አልተሳሳታችሁም። ከምስክር ወረቀት አንስቶ ገንዘብ ፤ ከፍ ሲልም እስከ መኪና ድረስ ያሉ ሽልማቶች ለአሸናፊዎች ሲበረከቱ ሁላችንም ተመልክተናል።
20 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቤት ሽልማት ግን እስካሁን አይተንም፣ ሰምተንም አናውቅም ብንል ማጋነን አይሆንብንም።
ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው የጂ ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ በቲክቶክ ገጻቸው ይዘት የሚፈጥሩ፣ ሰዎችን የሚያዝናኑ፣ የሚያስተምሩ፣ መድረኩን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም ማኅበረሰቡን የሚያግዙና የፈጠራ አቅማቸውን ሳይሰስቱ የሚያካፍሉ ቲክቶከሮችን በተለያዩ ዘርፎች በእጩነት አቅርቦ ሽልማት ሲያበረክት ቆይቷል። ባለፈው አመት በዝግጅቱ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የመኪና ስጦታ ለአመቱ ምርጥ ቲክቶከር የሸለመ ሲሆን ዘንድሮ ግን ስጦታውን ከምንግዜውም በላይ ከፍ አድርጎ በቤት ሽልማት ተመልሷል።
ይህ ሽልማት የዚህ ዓመት የዝግጅቱ አንደኛ ደረጃ ስፖንሰር በሆነው በድርጅታችን አማን ፕሮፐርቲስ እውን የሆነ ሲሆን ፣ በኢትዮጵያ የሽልማት ታሪክ ውስጥ ትልቁ ሽልማት የሆነውን 20 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቤት የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር ሆኖ ለሚመረጠው ሰው የምናበረክት ይሆናል።
የዘንድሮውን ሽልማት ለየት የሚያደርገው የ20 ሚሊዮን ብር የቤት ስጦታ መሆኑ ብቻ አይደለም። ቤቱ በመዲናችን አዲስ አበባ ከሚገኙ ዘመናዊ የመኖሪያ ሰፈሮች አንዱ በሆነው በብስራተ ገብርኤል የሚገኝ መሆኑና፣ የሚገነባውም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ በማስረከብ የሚታወቀው ድርጅታችን አማን ፕሮፐርቲስ መሆኑ ነው።
ይህንንም ዜና አርብ ፣ ጥቅምት 6 ቀን ሁለቱ ኩባንያዎች የስፖንሰርሺፕ ስምምነታቸውን በይፋ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ያጸደቁ ሲሆን፣ የ20 ሚሊዮን ብር የቤት ሽልማቱም በዚያው ዕለት ይፋ ሆኗል።
በዝግጅቱ ላይም የአማን ፕሮፐርቲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢኒያም ወንድሙ በአሁኑ ወቅት የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ በመምጣቱ ፣ መድረኩን ለበጎ ዓላማ የሚያውሉ እና በጎ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ወጣቶችን ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑን በማመን ድርጅታችን የዚህ ትልቅ ሽልማት አንደኛ ደረጃ ስፖንሰር ለመሆን መወሰኑን ተናግረዋል።
የድርጅታችን የማርኬቲንግ እና ሽያጭ ዳይሬክተር አቶ ዝናው አብዲ በበኩላቸው፣ “ቤት ማለት ቤተሰብን፣ ማህበረሰብን እና ሀገርን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ትልቅ እሴት ነው። በመሆኑም ለእነዚህ ወጣቶች ቤት ስንሸልም ሀገር እየሸለምናቸው እንደሆነ ሊታሰብ ይገባል” ብለዋል።
አክለውም አማን ፕሮፐርቲስ ከሪል እስቴት ልማት ባለፈ ትውልድ እና ሀገር በሚገነቡ ማህበራዊ ሁነቶች ላይ አዎንታዊ ተሳትፎ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
አማን ፕሮፐርቲስ ከዚህ ቀደም ያለውን የግንባታ ታሪክ እና የታማኝነት ጉዞ ካጠኑ እና ከገመገሙ በኋላ የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር የሚሆነውን ሰው እንዲሸልም እንደመረጡት የቅርንፉድ ኤቨንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር መቅደም ደረጄ ገልጸዋል።
ይህ አጋርነት አማን ፕሮፐርቲስ ወጣቶችን ለመደገፍ እና ፈጠራን ለማበረታት የሚሄድበትን ርቀት የሚያሳይ ሲሆን የተሸላሚውንም ህይወት አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ልዩ ስጦታ ነው።
በያዝነው አመት በቦሌ፣ በሳር ቤት፣ በተክለሃይማኖት፣ በፒያሳ እና በሌሎችም ተመራጭ የመዲናዋ አካባቢዎች አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለደንበኞቻችን ለማቅረብ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን ሲሆን ድርጅታችን አማን ፕሮፐርቲስ እንደዚህ ባሉ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፉን እና ከወጣቶች ጎን መቆሙን ይቀጥላል።
የ2026 የጂ ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር በመሆን 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣውን ቤት ከአማን ፕሮፐርቲስ የሚረከበው ማን ይሆን?
አብረን የምናይ ይሆናል!
ለሁሉም ተሳታፊዎች መልካም እድል እየተመኘን የዕለቱን ጦማራችንን እናበቃለን።
በአማን ሰንብቱ!
Article not found
This article may have been moved or unpublished. Browse all articles.