Aman Properties blog

From the
Aman blog

Marketአማርኛ

አማን ፕሮፐርቲስ ሳር ቤት መግባቱን ሰምታችኋል?

20 October 2026 · 2 min read · Aman Properties

ወደ ዛሬው ጦማራችን ከመግባታችን በፊት ግን ሳር ቤት ለምን ሳር ቤት ተባለ?

 

ታሪኩ እንዲህ ነው…

 

በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት እንደ ከተማ ዳርቻ በሚቆጠረውና ጥቂት ህዝብ ብቻ ይኖርበት በነበረው አካባቢ፣ ሁለት ግዙፍ የሳር ክዳን ቤቶች ጎልተው ይታዩ ነበር። ቀስ በቀስ ታዲያ አገሬው እነዚያን ሳር ቤቶች እንደ ምልክት በመውሰድ “ሳር ቤቱ ጋር ነኝ” ፣ “ሳር ቤቱ ጋር ጠብቀኝ” እያለ ቦታ ለመጠቋቆም ይጠቀምበት ጀመረ። በጊዜ ሂደትም ሳር ቤት የአካባቢው መጠሪያ ለመሆን በቃ።

 

ዛሬ ላይ ሳር ቤት በዘመናዊ ህንጻዎች የተከበበ ስፍራ ቢሆንም፣ ትላንቱን ለመዘከር ያህል እነዛ ሁለት ግዙፍ ሳር ቤቶች እንደ አዲስ አሸብረቀው ዛሬም ድረስ ለታሪክ ቆመዋል።

 

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ…

 

አማን ፕሮፐርቲስ ከዚህ ቀደም በቦሌ ጋዜቦ፣ በብስራተ ገብርኤል፣ በካዛንቺስ፣ በካሬ ቆሬ እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ያስመዘገበውን ድንቅ የግንባታ ጥበብና ቁርጠኝነት ይዞ አሁን መዳረሻውን ሳር ቤት አድርጓል።

 

በኢትዮጵያ የሪልስቴት ዘርፍ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየጻፈ የሚገኘው አማን ፕሮፐርቲስ፣ ከአንድ አፓርትመንት የጀመረው ጉዞው እየሰፋ፣ ብዙዎችን የቤት ባለቤት እያደረገ፣ የዛሬዋን ብቻ ሳይሆን የነገዋንም አዲስ አበባ በሚመጥን የዲዛይን እና የጥራት ልክ እየተገለጠ ይገኛል።

 

ሳር ቤት ለምን ተመረጠ?

 

አማን ፕሮፐርቲስ የሚገነባባቸውን ቦታዎች ሲመርጥ እንዲሁ በአጋጣሚ አይደለም። "ቦታው ነገ ቤቱን ተረክበው ለሚኖሩበት ነዋሪዎች ይስማማል ወይ? የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸውን ያለ ምንም መጉላላት ማከናወን ይችላሉ ወይ? የትራፊክ ፍሰቱስ እንዴት ነው? ለገበያ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለመንግስት እና ለግል ተቋማት ያለው ርቀት ምን ያህል ነው?" የሚሉትን ጥያቄዎች ይጠይቃል ፤ ያጠናል።

 

ከሜክሲኮ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የበርካታ ኤምባሲዎች መገኛ የሆነው ሳር ቤት ይህንን ሁሉ ምቹ ሁኔታ በጥቅሉ የያዘ ስትራቴጂካዊ ስፍራ ነው። በቅርቡም በሜክሲኮ-ሳር ቤት የኮሪደር ልማት ይበልጥ ማሸብረቁ ተመራጭነቱን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።

 

ቤትን እንደ ኢንቨስትመንት ለሚመለከቱ ደንበኞችም ቢሆን ሳር ቤት ትክክለኛው ቦታ ነው። ከተለያየ አገራት የመጡ ዲፕሎማቶች እና የስራ ሀላፊዎች መኖሪያ አካባቢ በመሆኑ መልሶ ለመሸጥም ሆነ ለማከራየት እጅግ አዋጭ ነው።

 

አማን ፕሮፐርቲስ ቀጣይ መዳረሻውን ሳር ቤት ያደረገው ለዚሁ ነው። የሳር ቤትን ነባር ውበትና አዲስ ማንነት ከራሱ የኮንስትራክሽን ጥበብ ጋር አዋህዶ፣ ምርጥ ምርጡን ለደንበኞቹ እነሆ እያለ ይገኛል። 

 

የአማን ጉዞ ይቀጥላል!

 

ዛሬ ሳር ቤት መገኘቱን ቢያበስርም፣ በከተማዋ እምብርት ቦታዎች ላይ መገንባቱንና ማህበረሰቡን የቤት ባለቤት ማድረጉን ነገም አጠናክሮ ይቀጥላል። በአዲስ አበባ ተገድቦ አይቀርም፤ በክልል ከተሞች እንዲሁም ከባህር ባሻገር አድማሱን እያሰፋ በኢትዮጵያና በዓለም የሪልስቴት ዘርፍ የራሱን አሻራ ያሳርፋል።

 

ቀጣይ በሌላ ሳይት እና በሌላ ፕሮጀክት እንገናኛለን።

 

እስከዛው በአማን ይቆዩ!

← All articles

We are open

Talk to us today

Call, message or visit the sales office at Laphto Mall — we reply the same working day.

Call us
+251 945 59 59 59
Call short code
8077
WhatsApp
Message us
Email
info@amanpropertiesaddis.com
☎Call ✉WhatsApp ✎Book